ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሩዋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የሩዋንዳ መንግሥት ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት መገንቢያ ባስረከበው 7 ሺህ 7 መቶ 71 ካሬ መሬት ላይ  የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ  ናቸው፡፡ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በኪጋሊ የተበረከተው መሬት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ፍሬያማ እንዲሆን ይረዳል፡፡ ኢትዮጵያም ለሩዋንዳ ኤምባሲ መገንቢያ በአዲስ አበባ እኩል መጠን ያለው መሬት የሰጠች ሲሆን በኢትዮጵያና በሩዋንዳ መካከል ከአውሮፓውያኑ 2012 ጀምሮ 23 ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል።  እነዚህን በተሻለ ወደ ውጤት ለማስገባት የኢምባሲ ጽ/ቤት ግንባታ ቁልፍ ሚና አለው። ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ  ከሁለትዮሽ  ግንኙነት ባለፈ በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች አቋማቸውን በህብረት የሚያራምዱ ናቸው፡፡ ሩዋንዳ ከቅኝ ግዛት ለመውጣት ባደረገችው ተጋድሎ ወቅትም ሆነ ከአስከፊው ዘር ጭፍጨፋ በኋላ ኢትዮጵያ ቀድማ በመድረስ ለሩዋንዳውያን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጓ ይታወሳል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram